Back

ⓘ ታሪክ                                               

ታሪክ

ታሪክ በትክክል እንደሚሰፈን ከተጻፉት መዝገቦች አንስቶ ይጀምራል። ከዚያ አስቀድሞ ምንም የተጻፉት መዝገቦች ሳይኖሩ የነበረው ወቅት ቅድመ-ታሪክ ይባላል። በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም "ቅድመ-ታሪክ" ነው። በሌላ አገር ግን የጽሑፍ መዝገቦች እንዲሁም የታሪክ መጋረጃ መከፈቱ እንደ ግብጽ ጥንታዊ አይሆንም። ለምሳሌ ከሜክሲኮ ስሜን የኖሩት ስሜን አሜሪካ ኗሪዎች እንደ ብዙ አሕጉር ሰዎች ለረጅም ዘመን የጽሑፍ አካል ባጠቃላይ ያልነበራቸው ሆነው ቀሩ። ከዚሁ የመዝገቦች ጉድለት የተነሣ ከ1500 ዓም በፊት ያለው ጊዜ ሁሉ የስሜን አሜሪካ ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። ከ1500 ዓም በፊት የተቀረጹት አንዳንድ ጽሑፎች በተለይም የፊንቄ ቋንቋ በሰፊ በአሜሪካዎች ቢገኙም ሁላቸው በፈረንጅ ሊቃውንት አጠያያቂ ተብለዋል። ሆኖም ስለነዚህ የፊን ...

                                               

ቅድመ-ታሪክ

ቅድመ-ታሪክ ማለት ከታሪክ ወይም መዝገቦች ከተጻፉ በፊት ያለፈው ጊዜ ነው። በአለም ደረጃ መጀመርያው የታወቁት የጽሑፍ ቅርሶች ከ3125 ዓክልበ. ያሕል ሲሆኑ ከጥንታዊ ግብጽ ሥነ ቅርስ ታውቀዋል። ለምሳሌ የመንደሮቹ መኳያ ሰሌዳ እና የጊንጥ ዱላ ከዚህ ዘመን ናቸው። ስለዚህ ከ3125 ዓክልበ. በፊት ያለፈው ሁሉ የአለም "ቅድመ-ታሪክ" ነው። ከ3125 ዓክልበ. በፊት ደግሞ የድንጋይ ዘመን እየሆነ ከዚያ ወቅት ጀምሮ የናስ ዘመን ሆነ። ከግብጽ ውጭ፣ በሌሎች አገራት የቅድመ-ታሪክ መጨረሻና የታሪክ መጀመርያ የሚወሰንበት ጊዜ መዝገቦች ለመጻፍ የጽሕፈት ችሎታ በዙሪያው እንደ ታወቀ ይለያያል። ለምሳሌ በመስጴጦምያ ዙሪያ ታሪክ በ2400 ዓክልበ. ግድም ይጀምራል፤ ከዚያ በፊትም ቅድመ-ታሪክ ሊባል ይችላል። በአውሮጳ ግን ከሁሉ ቀድሞ ማንበብ የምንችልበት ጽሑፎች በ "ሚውኬናይ ጽሕፈት" ግሪክ አገር ከ1400 ዓክልበ. ግድም ናቸው። በአሜሪካዎችም በሜክሲኮ ዙሪያ ጽሕፈቶች ቢያንስ ከ900 ዓክልበ. ጀምሮ እንደ ታወቁ ቢመስልም፣ ከ300 ዓክልበ. በፊ ...

                                               

ሄሮዶቶስ

"ሂስቶሪያይ" ታሪኮች በሚባል ጽሑፍ 472 ዓክልበ. ገደማ ሄሮዶቶስ ስለ "ኢትዮጵያ" ጥንታዊ መረጃ አቅርቧል። በሄሮዶቱስ አስተያየት ኢትዮጵያ ከኤለፋንቲን ደሴት የአሁኑ አስዋን ጀምሮ ከግብጽ ወደ ደቡብ የሚገኘው አገር ሁሉ ነው። በወርቅ፣ የዝሆን ጥርስና ዞጲ እንጨት ሀብታም አገር ነው። አንድ ዋና ከተማ በሜሮዌ አላቸው፤ እዚያ አማልክታቸው ዜውስ እና ዲዮናስዮስ ብቻ ናቸው ይላል። በፈርዖን 1 ፕሳምቲክ ዘመን 650 ዓክልበ. ገደማ ብዙ የግብጽ ወታደሮች አገራቸውን ከደው በኢትዮጵያውያን መካከል እንደ ሰፈሩ ይላል። ከግብጽ 330 ፈርዖኖች፣ 18ቱ ኢትዮጵያውያን ማለት የኩሽ ፈርዖኖች ነበሩ ብሎ ጻፈ። ግዝረት ከሚፈጽሙት አገሮች አንድ መሆናቸውን ይመስክራል። የፋርስ ንጉሥ ካምቢስስ 570 ዓክልበ. ገደማ ሰላዮችን ወደ ኢትዮጵያውያን እንደ ላከ ሄሮዶቶስ ይነግረናል። ጠንካራና ጠንኛ ሕዝብ አገኙ። ካምቢስስ ከዚያ ወደ ኢትዮጵያ ቢዘምትም በቂ ስንቅ ባለማዘጋጀታቸው ለሥራዊቱ በፍጹም አልተከናወነምና ቶሎ ተመልሱ።

                                               

የሕገ መንግሥት ታሪክ

የሱመር ከተማ ላጋሽ አለቃ ኡሩካጊና በ2093 ዓክልበ. ያሕል ያዋጀ ሕገ ፍትሕ በታሪካዊ መዝገብ እስከምናውቀው ድረስ መጀመርያ የሕገ መንግሥት ሰነድ ነው። ሰነዱ እራሱ ገና አልተገኘም፤ ነገር ግን ለዜጎቹ አንዳንድ መብት እንደ ፈቀደላቸው ይታወቃል። ለምሳሌ ለመበለትና ለደሀ አደጎች ቀረጥ እንዳስቀረላቸው ድሆችንም ከሃብታሞች አራጣ እንደጠበቃቸው ይታወቃል። ከዚህ በኋላ ብዙ መንግሥታት በተጻፈ ሕግ እንዲገዙ ልዩ ስርዓት ነበራቸው። ከተገኙት ሕግጋት ሁሉ ጥንታዊ የሆነው በ1983 ዓክልበ. የገዙ የኡር ንጉሥ የኡር-ናሙ ሕግጋት ነው። በተለይ ዕውቅ የሆኑ የጥንት መንግሥት ሕጎች የኢሲን ንጉሥ ሊፒት-እሽታር ሕግጋት 1832 ዓክልበ. ፤ የኤሽኑና ሕግጋት ምናልባት 1775 ዓክልበ. ግድም፤ የባቢሎን ንጉሥ ሃሙራቢ ሕግጋት 1704 ዓክልበ. እና፤ ሕገ ሙሴ ለእስራኤል 1661 ዓክልበ. ናቸው። ሕገ ሙሴ በተለይ በኦሪት ዘጸአት 21 እና 22 ያህዌ አስተካክሎ ከነዚህ ሁሉ የተሻሸሉት ብያኔዎች ይጠቅልላል። በኋላ ኬጢያውያን 1488 ዓክልበ. ግድም እና ...

                                               

መምበርቱ

መምበርቱ ፈረንሳያውያን በአካዲያ መጀመርያ በሠፈሩበት ወቅት የሚግማቅ ብሔር ሳግሞው ነበሩ። መጀመርያ የገስፑጒትክ ክፍላገር ሳግሞው ሆነው፣ በኋላ የሌሎቹ 6 ሚግማቅ ክፍላገሮች ሳግሞዎች ዋና ሳግሞው እንዲሆኑ መረጡዋቸው። መምበርቱ ከስሜን አሜሪካ ኗሪዎች መጀመርያ የተጠመቁት በመሆናቸው በተለይ ይታወቃሉ። በሰኔ 20 ቀን 1602 ዓ.ም. ቄሱ አቤ ዠሴ ፍሌሼ ለመተባበር ምልክት እሳቸውን ስለ ፈረንሳይ ንጉሥ 4ኛ አንሪ ስም "አንሪ" ሰይሟቸው ከቤተሠባቸው ጋር አጠመቃቸው። ፈረንሳያውያን መጀመርያ በደረሱ ጊዜ በ1597 ዓ.ም. ዕድሜያቸው ከ100 አመት እንደ በለጠ ተብሎዋል። በወጣትነታቸው የፈረንሳይ ዠብደኛ ዣክ ካትዬን በ1526 ዓ.ም. ጉዞ ላይ መገኛነቱን ትዝ እንዳሉ ነገሯቸው። ፈረንሳያውያን ምሽግ በመምበርቱ አገር በፖርት ሮያል ሠርተው በ1599 ዓ.ም. ሁለት ሰዎች ብቻ ትተው ወጡ። በ1602 ዓ.ም. ወደ መምበርቱ እስከተመለሱ ድረስ እሳቸው ለምሽጉና ለ2ቱ ፈረንሳውያን ሰዎች ኅላፊና ታማኝ ነበሩ። ከተጠመቁ አስቀድሞ "ሳግሞው" ወይም ፖለ ...

                                               

ማርክሲስም-ሌኒኒስም

ማርክሲስም-ሌኒኒስም በተለይ በካርል ማርክስና በቭላዲሚር ሌኒን ትምህርት የተመሠረተ ፖለቲካዊ ርዕዮተ ዓለም ነው። ማርክሲስም-ሌኒኒስም የአንዳንድ መንግሥት ፍልስፍና በመሆኑ፣ በሃይማኖት ፈንታ እንደ የመንግሥት ሃይማኖት ያህል ያለ ሚና አጫውቷል። በአሁኑ ሰዓት በይፋ የማርክሲስት-ሌኒኒስት መንግሥት ያላቸው አገራት የሚከተሉ ናቸው፦ ኩባ - ከ1951 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል። የቻይና ሕዝባዊ ሪፐብሊክ - ከ1941 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1970 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም "ሶሻሊስም ከቻይናዊ ጸባይ ጋራ" ተብሏል። ቬትናም - ከ1937 ዓም ጀምሮ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1982 ዓም ይፋዊው ርዕዮተ ዓለም "የሆ ቺ ሚን ሃሣብ" ተብሏል። ላዎስ - ከ1967 ዓም ጀምሮ ርዕዮተ ዓለሙ ማርክሲስት-ሌኒኒስት ሆኗል። ስሜን ኮርያ - ከ1937 እስከ 1983 ዓም ድረስ በይፋ ማርክሲስት ሲሆን፣ ከ1964 ዓም ጀምሮ ከማርክሲስም የተደረጀው ርዕዮተ ዓለም "ጁቼ" ኰሙኒስም ተብሏል። በ1983 ዓም ደግሞ "ማርክሲስም" በይፋ ...

                                               

አፈ፡ታሪክ

አፈታሪክ ማለት ጥንት ወይም ሙሉ እውነታን መሰረት አደርጎ በመነሳት እየተለጠጠና ብሎም እየተንጋደደ በመጓዝ ከጭብጡ የሚርቅ ከፊል እውነት ወይም እውነታ ቢስ የሆነ ሰነድ ነው። ባላደጉ ሃገሮች ታሪክ መጽሃፍ ኣና ማስቅመጥ የተለመደ ኣልነበረም አባቶች ሃረጋውያን ከትውልድ ትውልድ ለልጆቻችቸው በተረትና ምሳሌ በቃል የሚሰተላልፉት አፈ ታሪከ በኣፍ የተተረከ እንጅ ያልተፃፈ ማለት ነወ።

መካከለኛ ዘመን
                                               

መካከለኛ ዘመን

መካከለኛው ዘመን በተለይ በአውሮፓ ታሪክ እንደሚወሰን ከ468 እስከ 1445 ዓም ድረስ ያህል ያለው ጊዜ ነው። ይህም ከ468 ዓም ወይም ከሮሜ ምዕራብ መንግሥት ውድቀት ለኦዶዋከር ጀምሮ ማለት ነው። መጨረሻውም ቁስጥንጥንያ ለኦቶማን ቱርኮች እስከ ወደቀበት ዓመት እስከ 1445 ዓም ድረስ ይቆጠራል። በዚህ ዘመን አብዛኛዎች አለም ሉል ሳይሆን ለጥ ያለ እንደ ነበረች ያምኑ ነበር።

ሲሞን ቦሊቫር
                                               

ሲሞን ቦሊቫር

ሲሞን ቦሊቫር የቬኔዝዌላ አለቃ ሲሆን ለብዙ ደቡብ አሜሪካ አገራት አብዮት በእስፓንያ መንግሥት ላይ ሠራ። የቬኔዝዌላ፣ እንዲሁም የግራን ኮሎምቢያ፣ የቦሊቪያ፣ እና የፔሩ መጀመርያ ፕሬዚዳንት ሆነ። የቦሊቪያ ስም ደግሞ ከ "ቦሊቫር" ደረሰ።

ቅዝቃዛው ጦርነት
                                               

ቅዝቃዛው ጦርነት

"ቅዝቃዛው ጦርነት" ከሁለተኛ ዓለማዊ ጦርነት በኋላ በተለይ ከአሜሪካና ሶቪዬት ሕብረት መካከል የነበረው መቀያየም ይገልጻል። ከ1937 እስከ 1982 ዓም ድረስ ያለው ዘመን ነው። እነዚህ ሁለት ኃይለኛ አገራት መቸም "የሞቀ ጦርነት" ስላልነበራቸው ዘመኑ "ቅዝቃዛው ጦርነት" በመባል ታውቋል። እንዲያም ሁለቱ የኑክሌር መሣሪያ ሃያላት በመሆናቸው ጦርነቱ "የሞቀ" ከሆነ እንደ ሆነ "እርግጠኛ እርስ በርስ መጥፋት" ይሆን ነበር። የተረፈው አለም ወይም ከአንድ ወይም ከሌላው ወገን ወዳጅ ስለ ሆነ የአለም መጥፋት ማለት ነበር። ሁለቱ አገራት ግን በዛቻ፣ በሰላይ፣ በሴራ፣ በወኪል ጦርነት ይታገሉ ነበር። በተለይ አሜሪካ በቬትናም ጦርነት፣ በኋላም የሶቭየት ኅብረት በአፍጋኒስታን ጦርነት ተዋጉ። የቅዝቃዛው ጦርነት ዘመን በሶቭየት ኅብረት ውድቀት በ1982 ዓም ያህል ጨረሰ።

                                               

የሐሳቦች ታሪክ በየክፍለዘመኑ

2400 ዓክልብ - ትክክለኛ ዘመን አቆጣጠር በግብጽ ፫ኛው ምዕተ ዓመት - የሰናዖር ሰዎች የኩኒፎርም አጻጻፍ እና የቁጥር ሥርዓት ፈጠሩ አንድ-አምላክ አምልኮ በግብጽ ዞራስተር የሰው ልጅ ህይወት በሁለት ኃይሎች ሰናይ እና እኩይ መካከል የሚካሄድ ትግል ነው አለ። ፪ኛው ምዕተ ዓመት 442 ዓክልብ - ኤምጶዴክለስ ሁሉም ነገር የተሰራው መሬት፣ ውሃ፣ አየር እና እሳት ከተባሉ ፬ ንጥረ ነገሮች ነው አለ ፬ኛው ክፍለ ዘመን - ዩክሊድ የጂኦሜትሪ መጽሐፉን ኤለመንትስ ጻፈ ፫ኛው ክፍለ ዘመን - ኤራጦስጤስ የምድርን ወገብ ርዝመት፤ እንዲሁም ከጸሐይ እና ከጨረቃ ያለውን ርቀት አሰላ። ፮-፭ኛው ክፍለ ዘመን - የብሉይ ኪዳን የመጀመሪያ አምስቱ መጻሕፍት በዕብራይስጥ ተጠናቀቁ ፩ኛው ምዕተ ዓምት 440 ዓክልብ - ዴሞክሪተስ የአቶምን ጽንሰ ሐሳብ አቀረበ

የኢንዱስትሪ አብዮት
                                               

የኢንዱስትሪ አብዮት

የኢንዱስትሪ አብዮት ማለት በተለይ ከ1750 እና 1820 ዓም ያህል መካከል የተከሠተው ለውጦች ዘመን ነው። በነዚህ አመታት ለውጦቹም የአዲስ ፈጠራዎችና ቴክኖሎጂዎች ፈጣን መስፋፋት ነበሩ። ከታላቅ ብሪታንያ ጀምሮ ተስፋፋ። የእንፋሎት ባቡርና የእንፋሎት ሃይል ተበዙ። የጋዝ ብርሃን፣ ሲሚንቶ ተደረጁ። የእጅ ሥራ ዘዴዎች በፋብሪካዎች ተተኩ። ጥንተ ንጥር ይጠቀም ነበር። ብዙ የብረት ክፍሎች የነበሯቸው ውስብስብ መኪናነቶች ተበዙ። እነዚህ ለውጦች የሕዝቦች ኑሮ ዘዴና ምቾት ከበፊት ዘመናት ይልቅ በጣም አሻሸሉ፣ የሕዝቦችም ቁጥር እንዲበዛ አስቻሉ።

የዓለም፡ታሪክ፡ከፍጥረት፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘመናችን፡ድረስ፡ 1834
                                               

የዓለም፡ታሪክ፡ከፍጥረት፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘመናችን፡ድረስ፡ 1834

የዓለም፡ታሪክ፡ከፍጥረት፡ጀምሮ፡እስከ፡ዘመናችን፡ድረስ፡ በ1834 ዓ.ም. በቄሱ ቻርለስ ዊሊየም ኢዘንበርግ የታተመ የታሪክ መጽሐፍ ነው። ይህ መጽሐፍ እና ሌሎች የአይዘንበርግ አማርኛ መጽሐፍት ከታተሙ በኋላ እየሩሳሌም ለነበር የኢትዮጵያ ስደተኞች የተሰጡ ሲሆን፣ ቆይተው የተነሱ የፕሮቴስታንት ሚሲዮኖች መጻሕፍቱን ወደ ሸዋ፣ መተማ፣ ጋፋት እና አድዋ አሰራጭተዋቸዋል። በዓፄ ቴዎድሮስ ቤተመንግስትም እንዲገኙ ተደርገዋል።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →