Back

ⓘ ቋንቋ
                                               

አዲስ ኪዳን

                                               

ሱቁጥራ

ሱቁጥራ ወይም ሶኮትራ በሕንድ ውቅያኖስ የሚገኝ የየመን ደሴት ነው። ባካባቢው ሦስት ሌሎች ትንንሽ ደሴቶችም አሉ። የሱቁጥራ ስም መነሻ ከሳንስክሪት /ድቪፐ ሱቀደረ/ "ሀሤት ደሴት" እንደ መጣ ይባላል። በ1ኛው ክፍለ ዘመን በተጻፈው ግሪክኛ የቀይ ባሕር ፔሪፕሉስ ጉዞ መግለጫ፣ ደሴቱ /ዲዮስኮሪዶ/ ወይም "የዲዮስኮሪ" መንታ ጣኦታት ተባለ። ሦስተኛው መነሻ አረብኛው /ሱቅ አል-ቃትራ/፣ "የጠብታ ሱቅ" እንደ ሆነ ይባላል። ጠብታ ማለት በሱቁጥራ ብቻ የሚገኘው የሱቁጥራ ሜርቆ ቀይ ፈሳሽ ሲሆን፣ ይህ ፈሳሽ ስለቀይ ቀለሙ ለማጌጥ ተፈላጊ ነበር። በጥንት የብዙ አገራት መርከበኞች እንደ ደረሱ ከጽሑፎቻቸው ብዛት ታውቋል። የደሴቱ ኗሪዎች በ44 ዓም በቅዱስ ቶማስ ተጠምቀው ወደ ክርስትና እንደ ገቡ ይነገራል። የኔስቶራዊ ቤተ ክርስቲያን ክፍልፋይ ምዕመናን ሆኑ። ከ10ኛው ክፍለ ዘመን ጀምሮ፣ በአሁኑ የመን የተገኘው ማህራ ሱልጣናት ሱቁጥራን ይገዙ ነበር። በ1499 ዓም የፖርቱጋል ጦር መርከቦች ሱቁጥራን ያዙት፣ ስላልተስማማቸው ግን በ1503 ዓም እን ...

                                               

ሴም

ሴም በብሉይ ኪዳንና በአይሁድ፣ ክርስቲያንና እስላም ሥነ ጽሑፍ ዘንድ በኖኅ መርከብ ላይ ከማየ አይኅ ካመለጡት ከኖኅ ሦስት ወንድ ልጆች መሃል አንዱ ነው። ወንድሞቹ ካምና ያፌት ነበሩ፤ ልጆቹም ኤላም፣ አሦር፣ አራም፣ አርፋክስድና ሉድ ናቸው። በመጽሐፈ ኩፋሌ ዘንድ ሴም በ1207 ዓ.ዓ. ተወለደ፤ በዚህ አቆጣጠር በ1308 ዓ.ዓ. ማየ አይኅ ወይም የጥፋት ውኃ በደረሰበት ዓመት የሴም ዕድሜ 101 ዓመት ያህል ነበር። ሚስቱም ሰደቀተልባብ ተብላ በመርከቡ ላይ ደግሞ አመለጠች። በስምምነት ሴም የተቀበለው የምድር ርስት ዕጣ በእስያ ከጢና ወንዝ ዶን ወንዝና ከግዮን ወንዝ አባይ ወንዝ መካከል ተገኘ። ስለ ሴም ሚስት ስም በሌሎች ልማዶች ውስጥ፣ ሚስቶች በኖህ መርከብ ላይ ይዩ። በኦሪት ዘፍጥረት 11:10 ዘንድ፣ ሴም 100 ዓመት ሲሆን ከጥፋት ውሃ 2 ዓመት በኋላ አርፋክስድን ወለደ፤ ከዚያ ሌላ 500 ዓመት ቆይቶ ባጠቃላይ 600 ዓመታት ኖረ። ይህ ከ2864 እስከ 2264 ዓመት ያህል ድረስ ከክርስቶስ ልደት በፊት ሊሆን ይችላል። በልማድ ዘንድ ...

                                               

ምዕተ ዓመት

ምዕተ ዓመት የአንድ መቶ ዓመት ጊዜ ነው። በእንሊዝኛው ሰንቹሪ ተብሎ የሚጠራ ሲሆን ሰንቲም ከሚለው ላቲን ቃል የተወሰደ ነው፤ ሰንቲም ማለት አንድ መቶ ማለት ነው። በሌላ መልኩ ደግሞ የአማርኛው መነሻ ግእዝ ሲሆን "ምእት" ከሚለው ቃል የተወሰደ ነው፤ "ምእት" ማለት በግእዝ ቋንቋ አንድ መቶ ማለት ነውና።

                                               

እስልምና

እስላም ሙስሊሙን አሊያም ሙስሊሚን ነው ፣ ሙስሊማ አንስታይ ሲሆን የርሱ ብዙ ቁጥር ሙስሊማት ነው። ኢስላም إِسْلَٰم ደግሞ ዲኑ ሲሆን 8 ጊዜ ተወስቷል። ወጅህ وَجَّهْ ሁለንተናን አሊያም ህላዌን የሚያሳይ ሲሆን የቃል ትርጉሙ *ፊት* ማለት ነው፣ አንድ ሰው ሁለንተናውን ለአላህ ሲሰጥ ታዛዥ፣ ተገዥ፣ አምላኪ ይባላል፣ ይህ በአረቢኛ *ሙስሊም* pማለት ነው፦ 2:112 እርሱ በጎ ሠሪ ኾኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ የሰጠ أَسْلَمَ ሰው ለርሱ በጌታው ዘንድ ምንዳው አለው፡፡ በነሱም ላይ ፍርሃት የለባቸውም፤ እነሱም አያዝኑም፡፡ 4:125 እርሱ መልካም ሰሪ ሆኖ ፊቱን وَجْهَهُ ለአላህ ከሠጠ أَسْلَمَ እና የኢብራሂምን መንገድ ቀጥተኛ ሲሆን፣ ከተከተለ ሰው፣ ይበልጥ ሃይማኖቱ ያማረ ሰው ማነው? 3:20 ቢከራከሩህም:- ፊቴን وَجْهِيَ ለአላህ ሰጠሁ أَسْلَمْتُ ፤ የተከተሉኝም ሰዎች እንደዚሁ ለአላህ ሰጡ በላቸዉ፤ የኢስላም አስኳሉ ተህሊል تهليل‎,ነው፣ ተህሊል ማለትም" ላ-ኢላሀ ኢልለሏህ”لا اله الاّ ...

                                               

መንፈስ ቅዱስ

መንፈስ ቅዱስ በክርስትና እምነት ከሥላሴ አንዱ ሲሆን የእግዚአብሔር መንፈስ ነው። መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ አእምሮ ያለዉ ማንነት ስሜት እና ፍቃድ ያለዉ እንደሆነ መፃፍ ቅዱስ ይናገራል መንፈስ ቅዱስ ስሜት አለው ያዝናል ኤፍ 4:30 መንፈስ ፈጣሪ ነው."የእግዛቤሬ መንፈስ ፈጠረኝ"እዮ 33:4 አብዛኛውን ጊዜ" መንፈስ” ተብለው የሚተረጎሙት ሩዋሕ የተባለው የዕብራይስጥ ቃልና ፕነቭማ የተባለው የግሪክኛ ቃል ብዙ ትርጉሞች አሏቸው። ሁሉም የሚያመለክቱት ለሰው ዓይን የማይታይንና በእንቅስቃሴ ላይ የሚገኝን አንድ ኃይል ነው። የዕብራይስጡና የግሪክኛው ቃላት የሚከተሉትን ነገሮች ለማመልከት ያገለግላሉ:- 1 ነፋስን፣ 2 በምድራዊ ፍጥረታት ውስጥ የሚሠራውን አንቀሳቃሽ የሕይወት ኃይል፣ 3 ከአንድ ሰው ምሳሌያዊ ልብ የሚወጣውንና አንዳንድ ነገሮችን በሆነ መንገድ እንዲሠራ ወይም እንዲናገር የሚያደርገውን አስገዳጅ ኃይል፣ 4 ከማይታይ ቦታ የሚመጡ መግለጫዎችን 5 ሕያው የሆኑ መንፈሳዊ አካላትን 6 አንቀሳቃሽ የሆነውን የአምላክ ኃይል ወይም መንፈስ ቅዱስ።

ቋንቋ
                                     

ⓘ ቋንቋ

ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋዎችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለመክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋዎች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ።

የሰው ልጅ ቋንቋ በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ህጻናት ቋንቋን በደመ ነፍስ ይማራሉ። በተፈጥሮ የሚገኙ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ከድምጽና ከየሰውነት ክፍሎች ምልክት ይፈጠራሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ የሰው ልጆች ቋንቋዎች ቢኖሩም የሁሉም የጋራ የሆኑ ቋሚ ጸባዮች አሏቸው። እኒህ ቋሚ ጸባዮች በሁሉም የተፈጥሮ ቋንቋውች ሠርጸው የሚገኙ እንጂ ላንዱ ሰርተው ላንዱ የማይሰሩ አይደሉም።

                                               

የቅጥ ቋንቋ

የ ቅጥ ቋንቋ ማለት በአንድ የሙያ ዘርፍ ጥሩ የንድፍ ተመክሮን በተስተካከለ ዘዴ መግለጽ ማለት ነው። ባህሪውም የሚከተለውን ይመስላል የተሰየመ ግብ ላይ ለመድረስ የሚያስችሉ መፍትሔዎች ቁልፍ ባሕሪያትን መግለጽ ቀልብ ያሳደሩበትን ተፈጥሮዋዊ ድክመቶችን ማስተዋልና መሰየም ነዳፊውን ከድክመት ወደ ድክመት ምክንያታዊ በሆነ መንገድ በደረጃ እንዲሄድ መርዳት በንድፉ ሂደቱ ብዙ መንገዶችን መፍቀድ