Back

ⓘ ቅድስት አርሴማቅድስት አርሴማ
                                     

ⓘ ቅድስት አርሴማ

ቅድስት አርሴማ ፣ ሂርፕሲም እንዲሁም ሪሂፕሲም ፣ ሪፕሲም ፣ አርብሲማ ወይም አርሴማ ተብላ የምትጠራ ሮማዊ መሰረት ያላት ሰማዕት ነበረች። እርሷ እና ባልደረቦችዋ የሰማዕትነት አክሊል የተቀዳጁ የመጀመሪያዎቹ የአርሜንያ ሰማዕታት እንደሆኑ ተደርገው ይታያሉ ።

እናታችን ከአባቷ ከቅዱስ ቴዎድሮስና ከእናቷ ቅድስት አትናሲያ በስዕለት ተወለደች ። ቤተሰቦቿ እግዚአብሔርን በቅንነት ያገለግሉ ከነበሩ ከከበሩ ካህናት ወገን እንደነበሩ የገድሏ መጽሐፍ ይነግረናል ። ሰማዕቷ ቅድስት አርሴማ ቅዱሳት መጻሕፍትን ከቤተሰቦቿ በሚገባ የተማረች፤ የተማረችውንም በተግባር የተረጎመች፤ በጸሎት ሕይወት የምትተጋ ከቅዱሳት አንስት አንዷ ናት ።

                                     

1. ገድልዋ እደሚያስረዳው

ድንግል እናታችን ቅድስት አርሴማን በምን እንመስላታለን? እርሷ በአድማስ ላይ ተቀምጦ እንደሚያበራ እንቁ ናትና ክብሯ ብዙ ነው ። መድኃኒታችን ክርስቶስ በወንጌል እንዳለው "በተራራ ላይ ያለች ከተማ ልትሠወር አይቻላትምና ።" የሰማዕቷ ሕይወት በፊታችን እንደ ብርሃን ተገልጦ ይታያል ። ቅድስት አርሴማ እንደ ልጅ ወላጆቿን በመታዘዝ ደስ ያሰኘች ቡርክት ናት ። ቅድስት አርሴማ ይሕ ቀረሽ የማይሏት ውብ ናት ። ቅድስት አርሴማ ድንግል ናት ። ቅድስት አርሴማ ባሕታዊት ጻድቅ ናት ። ቅድስት አርሴማ ኃያል ሰማዕት ናት ። ይሕስ እንደ ምን ነው ቢሉ፦ አበው በትውፊት እንደ ነገሩን ቅዱስ ጐርጐርዮስ የታላቋ ሰማዕት ቅድስት አርሴማ ትልቅ ወንድም ነው ። በዜና ሰማዕታት ተጽፎ እንደሚገኘው በዚያ የመከራ ዘመን ቅዱስ ጐርጐርዮስ ሦስት ኃላፊነቶች ነበሩበት ።

  • ፫.የሚመጣውን መከራ ለመቀበል ራሱን ማዘጋጀት ።
  • ፪.ትምህርተ ቤተ ክርስቲያንን በሚገባ ማጥናት ።
  • ፩.ቅድስት አርሴማን ጨምሮ ደናግሉን ማጽናት ።

ቅዱሱ ሦስቱንም ኃላፊነቶች በሚገባ በመወጣቱ ከራሱ አልፎ ለሌሎቹ አርአያ መሆን ቻለ ። ያቺን ንጽሕት አርበኛ ቅድስት አርሴማንም አጽንቶ የደናግሉ መሪ አደረጋት ። መከራው በጣም ገፍቶ እስከ መጣበት ጊዜ ድረስ በአንድ የደናግል ገዳም ውስጥ ሆነው ይጸልዩ፣ ይጾሙ ፣ ገዳማዊ ሥራንም ይሠሩ ነበር ። ለዚህም ነው ቅድስት አርሴማና ቅዱስ ጐርጐርዮስ ጻድቃን የምንላቸው ። በኋላ ግን ማኅደረ ሰይጣን ዲዮቅልጢያኖስ በመልኳ ተማርኮ ቅድስት አርሴማን ካላገባሁ በማለቱ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ድንግሏን አርሴማን ጨምሮ መቶ ሃያ ሰባት ክርስቲያኖችን ይዞ ወደ አርማንያ ተሰደደ ። በአርማንያም በአንድ ገዳም ውስጥ ተደብቀው በጾምና በጸሎት ለጥቂት ጊዜ ቆዩ፤ ነገር ግን ረሃብ ፈጃቸው ። የሚላስ የሚቀመስ ነገር በአካባቢው ባለ መኖሩ ቅዱስ ጐርጐርዮስ ወደ ከተማ ለመውጣት ተገደደ ። በዚያም በድርጣድስ ቤተ መንግስት ውስጥ ባርነት ተቀጠረ ። በሚያገኛት ገንዘብም ወገኖቹን ይረዳ ነበር። መከራው ግን አለቀቃቸውም ። ርጉም ዲዮቅልጢያኖስ ቅዱሳኑ ወደ አርማንያ መሔዳቸውን ስለ ሰማ ይዞ እንዲልክለት ድርጣድስን ላከበት ። ድርጥዳስ ግን ለራሱ ፈለጋት ።

                                     

2. የሰማዕትነትዋ መነሻ

ይቺ ታላቅ ሰማዕት በነበረችበት ዘመን በአርመን የነገሠው አረማዊ ንጉሥ ይኸው ድርጣድስ ይባላል፡፡ ይህ ንጉሥ እግዚአብሔር አምላክ በሙሴ ላይ አድሮ "ቀልጠው የተሠሩትን የአማልክት ምስሎች ለአንተ አታድርግ" ብሎ የተናገረውን በመቃወም ለጣዖት የሚሰግድ ፀሐይንም ያመልክ ነበር ዘጸ.፴፬ ቁ.፲፯ ፡፡ በዘመኑ የነበሩ ክርስቲያኖችን "እኔ ለማመልከው "አምላክ" ወይም ጣዖት መስገድ አለባችሁ ፤ ይህን የማታደርጉ ከሆነ ትእዛዜን ጥሳችኋልና መከራ ይጸናባችኋል" የሚል ዐዋጅ በማውጣት ክርስቲያኖች ለስቃይ እዲጋፈጡ ሆነ ፡፡ ጨካኙ ንጉሥ ድርጣድስ ይህን ትእዛዙን ባለማክበራቸው መከራና ስቃይ ያደረሰባቸው ክርስቲያኖች ቁጥራቸው ፻፳፯ ነበር ።

                                     

3. የቅድስት አርሴማ ውሳኔ

ቅድስት አርሴማም ይህን አይታ ከክርስቲያን ወገኖችዋ ጋር ወግና ስለክርስቶስ መመስከር ጀመረች ። የንጉሡም አገልጋይ በደም ግባቷና በንግግሯ ማማር ተደንቆ በዚች በፈቃዷ ሰማዕትነትን ልትቀበል በወደደች ሴት ምንም ሊያደርግባት ስላልወደደ ወደ ንጉሡ ወደ ድርጣድስ ከሃያ ሰባቱ ክርስቲያኖች ጋር ወሰዳት ፡፡ ንጉሡም ብዙ የተነገረላትን ወጣት ሲያይ በውበቷና በንግግሯ ተማርኮ ለዓለማዊ ደስታውና ፍላጎቱ ተመኛት ፡፡ ሚስት ትሆነው ዘንድ አብዝቶ ተማጸናት ፡፡ እጅ መንሻና ማታለየ የዚህን ዓለም ወርቅና ብር አቀረበላት ፡፡ ቅድስት አርሴማ ግን መልክ ረጋፊ ፤ የዚህ ዓለም ሀብትም ከንቱ እንደሆነ ስለምታውቅ በዓላማዋ ጸናች! ንጉሡንም "እኔ የንጉሥ ክርስቶስ ሙሽራ እንጂ የዚህን ዓለም አላፊ ጠፊ የሆነውን ገንዘብና ደስታ የምሻ አይደለሁም ፡፡" በማለት መለሰችለት ፡፡

                                     

4. የንጉሡም መልስና ዕድሉ

ይህን በሰማ ጊዜ ሊያስፈራራትም ሞከረ ። ዓይኑዋ አያየ ደናግሉን ጨፈጨፋቸው ። ኣልሳካልህ ቢለው በኣደባባይ በግድ ሊያገባት ቢሞከር እጁን ጠምዝዛ በሰው ሁሉ ፊት መሬት ላይ ጣለችው ። እጅግ ስላፈረ ኣስገረፋት ኣሰቃያት ኣይኑዋንም አወጣ ። በመጨረሻም አንገቱዋን አስቆርጦ ከሰማዕታቱ ጋር ተራራ ላይ ጣላት ። ከነገሩ ሁሉ በህዋላ ድርጣድስና ባለምዋሎቹ ለኣደን በሔዱበት እርኩስ መንፈስ ወደ ኣውሬነት ቀየራቸው ። የንጉሱ እንሰሳ አውሬ መሆን በአርሜኒያ ታላቅ ድንጋጤ ፈጠረ ። የንጉሡ እህት ስታለቅስ በራዕይ ተገልጾላት ጎርጎሪዮስን ከተቀበረበት ካላወጣቹህ አትድኑም ኣለቻቸው ። ወዲያውም ቆፍረው አወጡት ። ቅዱሱ እንደወጣ ዕረፍት አልፈለገም ፣ ለአስራ አምስት ዓመታት ቀባሪ አጥቶ የተበተነውን የቅድስት አርሴማና የ ሰማዕታቱን አጽም ሰብስቦ በክብር አኖረው ።ድርጣድስና ባለምዋሎቾንም ወደ በርሃ ሔዶ ፈወሳቸው ።

የቅድስት አርሴማ አጽም በአስራ አራተኛው ክፍለ ዘመን ከሌሎች ሰማዕታት አጽም ጋር ወደ ኢትዮጵያ እንደመጣ አባቶቻችን በትውፊት ይናገራሉ ።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →