Back

ⓘ ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፩፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፩
                                     

ⓘ ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ፩

፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ በአዲስ ኪዳን ሁለተኛው መልዕክት ሲሆን ቅዱስ ጳውሎስ በቆሮንጦስ እያለ በ፶ ዎቹ ዓ.ም. ለቆሮንጦስ ሰዎች የጻፈው የመጀመሪያ መልዕክት ነው ። ፲፮ ምዕራፎች ይይዛል ። ይህ ፩ኛ ምዕራፍ ሲሆን በ፴፩ ንዑስ ክፍሎች ይከፈላል ።

ቅዱስ ጳውሎስ ለቆሮንጦስ ሰዎች መልዕክት የጻፈበት ምክኒያት ብዙ ናቸው ለምሳሌ ትንሳዔ ሙታን የለም እስከማለት የደረሱ ነበሩ እንዲሁም በቆሮንቶስ ምዕመናን መሀከል ፣ እኔ የጳውሎስ ነኝ ፣ እኔ የአጵሎስ ነኝ ፣ የኢየሱስ ነኝ.እያሉ መከፋፈላቸውን ሰምቶ ከዚህ ስህታቸው እንዲታረሙ ፤ በተጨማሪም ዓለምን ለማሳፈር እግዚአብሔር ታላቁን ሚሥጥር በዓለም በተናቁት ሰዎች እንዲገለፅ ማድረጉን ለማሳወቅ ጻፈው ።

የሐዋርያው ጳውሎስ መልዕክት ፩ኛ ወደ ቆሮንጦስ ምዕራፍ ፩

                                     

1. ቁጥር ፩ - ፲

1፤በእግዚአብሔር፡ፈቃድ፡የኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ሐዋርያ፡ሊኾን፡የተጠራ፡ጳውሎስ፣ ወንድሙም፡ሶስቴንስ፥ 2፤በቆሮንቶስ፡ላለች፡ለእግዚአብሔር፡ቤተ፡ክርስቲያን፥በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ ለተቀደሱት፥ የእነርሱና፡የእኛ፡ ጌታ፡የኾነውን፡የጌታችንን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡ስም፡በየስፍራው፡ከሚጠሩት፡ዅሉ፡ ጋራ፡ቅዱሳን፡ለመኾን፡ ለተጠሩት፤ 3፤ከእግዚአብሔር፡ከአባታችን፡ከጌታም፡ከኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ጸጋና፡ሰላም፡ለእናንተ፡ ይኹን። 4፤በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡ስላመናችኹ፡በተሰጣችኹ፡በእግዚአብሔር፡ጸጋ፡ምክንያት፡ ዅልጊዜ፡ስለ፡እናንተ፡ አምላክን፡አመሰግናለኹ፤ 5-6፤ለክርስቶስ፡መመስከሬ፡በእናንተ፡ዘንድ፡እንደ፡ጸና፥በነገር፡ዅሉ፣በቃልም፡ ዅሉ፣በዕውቀትም፡ዅሉ፡ በርሱ፡ባለጠጋዎች፡እንድትኾኑ፡ተደርጋችዃልና። 7፤እንደዚህ፡የጌታችንን፡የኢየሱስ፡ክርስቶስን፡መገለጥ፡ስትጠባበቁ፡አንድ፡የጸጋ፡ ስጦታ፡እንኳ፡ አይጐድልባችኹም፤ 8፤ርሱም፡ደግሞ፡በጌታችን፡በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ቀን፡ያለነቀፋ፡እንድትኾኑ፡እስከ፡ ፍጻሜ፡ድረስ፡ ያጸናችዃል። 9፤ወደልጁ፡ወደጌታችን፡ወደኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ኅብረት፡የጠራችኹ፡እግዚአብሔር፡ የታመነ፡ነው። 10፤ነገር፡ግን፥ወንድሞች፡ሆይ፥ዅላችኹ፡አንድ፡ንግግር፡እንድትናገሩ፡ባንድ፡ልብና፡ ባንድ፡ዐሳብም፡ የተባበራችኹ፡እንድትኾኑ፡እንጂ፡መለያየት፡በመካከላችኹ፡እንዳይኾን፡በጌታችን፡ በኢየሱስ፡ክርስቶስ፡ስም፡ እለምናችዃለኹ።

                                     

2. ቁጥር ፲፩ - ፳

11፤ወንድሞቼ፡ሆይ፥በመካከላችኹ፡ክርክር፡እንዳለ፡ስለ፡እናንተ፡የቀሎዔ፡ቤተ፡ሰዎች፡ አስታውቀውኛልና። 12፤ይህንም፡እላለኹ፦እያንዳንዳችኹ፦እኔ፡የጳውሎስ፡ነኝ፥እኔስ፡የአጵሎስ፡ነኝ፥እኔ፡ ግን፡የኬፋ፡ነኝ፥እኔስ፡የክርስቶስ፡ነኝ፡ትላላችኹ። 13፤ክርስቶስ፡ተከፍሏልን፧ጳውሎስስ፡ስለ፡እናንተ፡ተሰቀለን፧ወይስ፡በጳውሎስ፡ስም፡ ተጠመቃችኹን፧ 14-15፤በስሜ፡እንደ፡ተጠመቃችኹ፡ማንም፡እንዳይል፡ከቀርስጶስና፡ከጋይዮስ፡በቀር፡ ከእናንተ፡አንድን፡እንኳ፡ስላላጠመቅኹ፡እግዚአብሔርን፡አመሰግናለኹ። 16፤የእስጢፋኖስንም፡ቤተ፡ሰዎች፡ደግሞ፡አጥምቄያለኹ፤ጨምሬ፡ሌላ፡አጥምቄ፡እንደ፡ ኾነ፡አላውቅም። 17፤ለማጥመቅ፡ክርስቶስ፡አልላከኝምና፥ወንጌልን፡ልሰብክ፡እንጂ፤የክርስቶስ፡መስቀል፡ ከንቱ፡እንዳይኾን፡በቃል፡ጥበብ፡አይደለም። 18፤የመስቀሉ፡ቃል፡ለሚጠፉት፡ሞኝነት፥ለእኛ፡ለምንድን፡ግን፡የእግዚአብሔር፡ ኀይል፡ነውና። 19፤የጥበበኛዎችን፡ጥበብ፡አጠፋለኹ፡የአስተዋዮችንም፡ማስተዋል፡እጥላለኹ፡ተብሎ፡ ተጽፏልና። 20፤ጥበበኛ፡የት፡አለ፧ጻፊስ፡የት፡አለ፧የዚች፡ዓለም፡መርማሪስ፡የት፡አለ፧እግዚአብሔር፡የዚችን፡ ዓለም፡ጥበብ፡ሞኝነት ፡ እንዲኾን፡አላደረገምን፧

                                     

3. ቁጥር ፳፩ - ፴፩

21፤በእግዚአብሔር፡ጥበብ፡ምክንያት፡ዓለም፡እግዚአብሔርን፡በጥበቧ፡ስላላወቀች፥በስብከት፡ሞኝነት፡ የሚያምኑትን፡ሊያድን፡የእግዚአብሔር፡በጎ፡ፈቃድ፡ኾኗልና። 22፤መቼም፡አይሁድ፡ምልክትን፡ይለምናሉ፡የግሪክ፡ሰዎችም፡ጥበብን፡ይሻሉ፥ 23፤እኛ፡ግን፡የተሰቀለውን፡ክርስቶስን፡እንሰብካለን፤ይህም፡ለአይሁድ፡ማሰናከያ፡ለአሕዛብም፡ ሞኝነት፡ነው፥ 24፤ለተጠሩት፡ግን፥አይሁድ፡ቢኾኑ፡የግሪክ፡ሰዎችም፡ቢኾኑ፥የእግዚአብሔር፡ኀይልና፡ የእግዚአብሔር፡ጥበብ፡የኾነው፡ክርስቶስ፡ነው። 25፤ከሰው፡ይልቅ፡የእግዚአብሔር፡ሞኝነት፡ይጠበባልና፥የእግዚአብሔርም፡ድካም፡ከሰው፡ይልቅ፡ ይበረታልና። 26፤ወንድሞች፡ሆይ፥መጠራታችኹን፡ተመልከቱ፤እንደ፡ሰው፡ጥበብ፡ጥበበኛዎች፡የኾኑ፡ብዙዎች፥ ኀያላን፡የኾኑ፡ብዙዎች፥ባላባቶች፡የኾኑ፡ብዙዎች፡አልተጠሩም። 27፤ነገር፡ግን፥እግዚአብሔር፡ጥበበኛዎችን፡እንዲያሳፍር፡የዓለምን፡ሞኝ፡ነገር፡መረጠ፤ብርቱንም፡ነገር፡ እንዲያሳፍር፡እግዚአብሔር፡የዓለምን፡ደካማ፡ነገር፡መረጠ፤ 28፤እግዚአብሔርም፡የኾነውን፡ነገር፡እንዲያጠፋ፡የዓለምን፡ምናምንቴ፡ነገር፡የተናቀውንም፡ነገር፡ ያልኾነውንም፡ነገር፡መረጠ፥ 29፤ሥጋን፡የለበሰ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡እንዳይመካ። 30-31፤ነገር፡ግን፦የሚመካ፡በእግዚአብሔር፡ይመካ፡ተብሎ፡እንደተጻፈው፡ይኾን፡ዘንድ፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ጥበብና፡ጽድቅ፣ቅድስናም፣ቤዛነትም፡በተደረገልን፡በክርስቶስ፡ኢየሱስ፡የኾናችኹ፡ከርሱ፡ነው።

Free and no ads
no need to download or install

Pino - logical board game which is based on tactics and strategy. In general this is a remix of chess, checkers and corners. The game develops imagination, concentration, teaches how to solve tasks, plan their own actions and of course to think logically. It does not matter how much pieces you have, the main thing is how they are placement!

online intellectual game →